ኢትዮጵያ ተነሥታለች፤ ከእንግዲህ ወደ ኋላ አትመለስም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ተነሥታለች፤ ከእንግዲህ ወደ ኋላ አትመለስም ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ የማንሠራራት ቀንን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት ይሄ የኢትዮጵያ ማንሠራራት ጉዞ በዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የታገዘ መሆን አለበትም ብለዋል፡፡
በተለይም በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ በአምራችነትና በአይሲቲ ዘርፎች የላቁ ውጤቶችን እያስመዘገብን መቀጠል አለብን ነው ያሉት፡፡
ለዕድገታችን አጋዥ የሚሆን ሀብት መፍጠር እና ገቢ መሰብሰብ ይገባናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ዕድገታችን የሚያመነጨውን ገቢና ሀብትም በሚገባ ሰብስበንና ቆጥበን ለብልጽግና ግባችን መጠቀም አለብን ብለዋል፡፡
የጀመርነውን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በማሣለጥና በማሳካት የኢትዮጵያ ማንሠራራት ወደ ዘላቂ የኢትዮጵያ ብልጽግና እንዲለወጥ እናደርጋለን ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ተናግረዋል፡፡
0 Comments