Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ተቋሙ ለግብር ከፋዮች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር መደበኛ የስራ ሰዓቱን እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት አራዝሟል-አቶ ያሲን አብዱላሂ

የሀረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ለግብር ከፋዮች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር መደበኛ የስራ ሰዓቱን እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ማራዘሙን የቢሮው ሀላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ መደበኛ የስራ ሰዓቱን እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ማራዘሙን አስታወቀ።

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂ እንደገለፁት የሰዓት ማሻሻያው ለግብር ከፋዮች ምቹ ሁኔታ መፍጠርን ታሳቢ ያደረገ ነው።

በዚህም ተቋሙ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ባሉት ቀናት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ድረስ መደበኛ አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

ይህም ግብር ከፋዩ በተመቸው ሰዓት ግብሩን እንዲከፍል በማስቻል በስራ መደራረብ ምክንያት ግብር ባለ መክፈሉ ምክንያት ለቅጣት እንዳይዳረግ የሚያስችል መሆኑን አክለዋል።

የሚጠበቅባቸውን ዓመታዊ ግብር የከፈሉ ግብር ከፋዮችን በማመስገን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር ከፋዮች የመክፈያ ግዜው ከመጠናቀቁ በፊት ግብር በወቅቱ በመክፈል ግዴታቸውን እንዲወጡም አቶ ያሲን አብዱላሂ መልዕክት አስተላልፈዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

aoAfaan Oromo