Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ባለፉት 6 ወራት ከተማዋን ለነዋሪዎቿ እና ለጎብኚዎች ምቹ ምቹ በማድረግ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል-አቶ ኢሊያስ ዮኒስ

ሀረር፤ ጥር 21/2017 (ሀክመኮ)፦ባለፉት 6 ወራት የሀረር ከተማን ለነዋሪዎቿ እና ለጎብኚዎች ምቹ በማድረግ አበረታች ውጤት መመዘገቡን የከተማው ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኢሊያስ ዮኒስ ገለፁ።

የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ባለፉት 6 ወራት 

ከተማዋን አረንጓዴ፣ውብና ጽዱ ከማድረግ አንፃር አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ።

የከተማው ማዘጋጃ ቤት  ስራ አስኪያጅ አቶ ኤልያስ ዮኒስ እንደገለጹት፥ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድን በማሳለጥ እና አረንጓዴ እና መናፈሻ ስፍራዎችን በማስፋት ከተማዋን ለነዋሪዎቿ እና ለጎብኚዎች አረንጓዴ ውብና ጽዱ የማድረግ ስራ ተከናውኗል።

ከጽዳት ጋር በተያያዘ በቀን ሶስት ጊዜ የደረቅ ቆሻሻን በማንሳት ከተማዋን ጽዱ የማድረግ ሰራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አመልክተዋል። 

በተለይም ከደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና መልሶ ከመጠቀም አኳያ በማህበር የተደራጁ ወጣቶችና ሴቶችን ወደ ስራ በማስገባት ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ የከተማዋን ንጽህና የመጠበቅ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በዚህም በዘርፉ ለተሰማሩ ስድስት ማህበራትና  እና 800 ለሚሆኑ ሴቶች የስራ እድል መፈጠሩንም አቶ ኤልያስ ጠቅሰዋል።

በከተማው የአረንጓዴ ስፍራዎችንና መናፈሻዎችን  ከማስፋት አንጻርም በከተማዋ ማዘጋጃ ቤትና በግለሰቦች የተለያዩ ድጋፍ የአረንጓዴ ስራዎችና የመናፈሻዎች ስራ መከናወናቸውን ተናግረዋል።

ከተማዋን ውብ ከማድረግ አንጻርም ከዚህ ቀደም አገልግሎት አቋርጠው የነበሩ ከአንድ ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ዳር መብራቶች ተጠግነው ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን ገልጸዋል።

በከተማው የሚታየውን ህገ ወጥነት ከመከላከል አንጻር በግማሽ በጀት ዓመቱ  በጎዳና እና መንገድ ዳር ግብይት የሚፈጽሙ 2ሺህ 261 ህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ መንገዶችን ለእግረኛና ተሽከርካሪ ክፍት እንዲሆኑ የማድረግ ስራ መከናወኑን ገልጸዋል።

በከተማው በህገ ወጥ መንገድ የተወረረን 2 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት እንዲመለስ መደረጉንም አክለዋል።

እንደ አቶ ኤልያስ ገለጻ፥ በከተማው ነዋሪውንና ጎብኚውን  የሚያረካና ከተማዋን ወደ ተሻለ ደረጃ  የሚያሸጋግሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ይሆናሉ።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

aoAfaan Oromo