በ 2017 በጀት ዓመት የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማጎልበት ይሰራል-ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር
በሀረሪ ክልል በ 2017 በጀት ዓመት የተመዘገቡ ስኬቶችን ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰራ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር ገለፁ።
በሀረሪ ክልል የመንግስትና የፓርቲ የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀመረ ።
በመድረኩ ላይም የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም እስከ ወረዳ ያሉ የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።
በግምገማ መድረኩ ማስጀመሪያ ላይ የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር እንደገለፁት በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት በክልሉ በሁሉም ዘርፎች አበረታች ተግባራትን ማከናወን ተችሏል።
በተለይ በክልሉ ማህበራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊ እንዲሁም በከተማ ልማት ዘርፍ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራትን ማከናወን መቻሉን ገልፀዋል።
በበጀት ዓመቱ የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ለማህበረሰቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ተጨባጭ ለውጥ የተመዘገበበት መሆኑንም አክለዋል።
የግምገማ መድረኩም በበጀት ዓመቱ የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስፋት የተስተዋሉ ውስንነቶችን በመሙላት የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስፋት ግብዓት በመሰብሰብ ዝግጅት የሚደረግበት መሆኑን ጠቁመዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሮዛ ኡመር ፣የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፣ የሀረሪ ብሄራዊ ጉባኤ አፈ ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድን ጨምሮ የክልሉ የመንግስትና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ ዓመራሮች እየተሳተፉ ነው።
የግምገማ መድረኩ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑም ተመላክቷል።
0 Comments