Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በጁገል አለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የሚታዩ ያዘመሙ ፖሎች እና ውስብስብ የቴሌ መስመሮች ስጋት ደቅኖብናል – የሀረር ከተማ ነዋሪዎች

በጁገል አለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የተዘረጉ የቴሌ ፖሎች እና ውስብስብ መስመሮች ስጋት መደቀኑን የሀረር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ

ቅሬታቸውን የገለፁ የከተማው ነዋሪዎች እንዳሉት በተለይም አለም አቀፉ የጁገል ቅርስ ውስጥ የሚገኙና ከእድሜ ብዛት ያዘመሙ ፖሎች ከመቼ መቼ ወደቀብን እያልን በስጋት ላይ እንገኛለን።

ያረጁና ያዘመሙ እርስ በዕርስ ተደጋግፈው የሚገኙ አለፍ ሲልም ቅርሱን ተደግፈው የሚስተዋሉ ፖሎች በሰዎች ብሎም በመኖሪያ ቤቶች ላይ እንዳይወድቁ ስጋት እንዳላቸው ነው ነዋሪዎቹ የገፁት።

በጁገል ውስጥ ለውስጥ እና ዙሪያ የተከናወነው የማስዋብና ቅርስን የመንከባከብ ስራ ቅርሱ እንዲጠበቅና የተለየ ውበት እንዲላበስ ያደረገ ቢሆንም እነኚህ ያዘመሙ ፖሎችና ውስብስብ ገመዶች አለም አቀፉን የጁገል ቅርስ ገፅታ እንዲበላሽ እያደረገ መሆኑን ነዋሪዎቹ አክለዋል።

ችግሩ መፍትሔ ያገኛል ብለን ብንጠብቅም አሁንም ስጋትነቱ መቀጠሉን ጠቁመው ተቋሙ የተወሳሰቡ መስመሮችን እና ለመወደቅ የተቃረቡ ፖሎችን ስርዓት በማስያዝ ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያበጅ ጠይቀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

aoAfaan Oromo