Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ የተማሪ ውጤትን ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ተመልክተናል – ሚኒስቴር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ

በሀረሪ ክልል የተማሪ ውጤትን ለማሻሻል አበረታች ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን መመልከት መቻላቸውን የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ ገለፁ።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ በሀረሪ ክልል የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን ተመልክተዋል።

ሚኒስቴር ዴኤታዋ በመስክ ምልከታው ወቅት እንደገለፁት በክልሉ በ12ኛ ክፍል የተመዘገበውን ውጤት የበለጠ ለማሻሻል በቁርጠኝነት ወደ ስራ መገባቱን መመልከታቸውን ገልፀዋል።

የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ከመደበኛው ትምህርት በተጨማሪ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርቶችን እንዲወስዱ በመደረግ ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በተለይ መምህራኑ ተማሪዎችን በተለያዩ ጊዜያት በመመዘን አስፈላጊውን ድጋፍ እና እገዛ እያደረጉላቸው መሆኑን በመስክ ምልከታው መገንዘባቸውን ገልፀዋል።

በክልሉ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን በመጠቆም በማህበረሰብ ተሳትፎ ለመምህራን የመኖሪያ ቤቶች መገንባታቸውንም ጠቁመዋል።

በክልሉ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የተጀመሩ አበረታች ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ገልፀዋል።

በክልሉ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተማሪ መማሪያ መፅሀፍት በተገቢው መልኩ ተደራሽ ሆኖ ተማሪዎች እየተጠቀሙበት መሆኑ እና የቤተ መፅሀፍት አገልግሎቱ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን መመልከታቸውንም አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል በክረምት በጎ ፈቃድ ስራ የተማሪ ወላጆች ላይ ሊደርስ የሚችለውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቀነስ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መበርከቱንም አስረድተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ አበርክተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

aoAfaan Oromo