በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራት የስራ ዕድል ተጠቃሚነታችንን አሳድጓል – የስራ ዕድል ተጠቃሚዎች
በሀረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራት የስራ ዕድል ተጠቃሚነታችንን አሳድጓል ሲሉ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የስራ እድል የተፈጠረላቸው ዜጎች ተናገሩ
የስራ ዕድል ተጠቃሚ ዜጎቹ በሰጡት አስተያየት እንደገለፁት በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ተግባራት ቀጣይነት ያለው የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንድንሆን አስችሎናል።
በተለይም መንግስት የጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ከማድረግ በተጨማሪ በርካታ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
እኛም በተፈጠረልን የስራ ዕድል የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ከመሆን ባሻገር በልማቱ ላይ አሻራችንን በማኖራችን እድለኝነት ይሰማናል ብለዋል።
በተለይ የልማት ስራው በምሽት ጭምር እየተከናወነ እንደሚገኝና በተፈጠረላቸው የስራ ዕድል ከቀን በተጨማሪ በምሽት በመስራት የተሻለ ገቢ እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም በልማቱ ተሰማርተን ቤተሰባችንን መምራት የሚያስችለንን ገቢ በማግኘት ተጠቃሚ አድርጎናል።
ካሁን ቀደም ስራ ሳያገኙ ቀናቶችን ያሳልፉ እንደነበር በማስታወስ የኮሪደር ልማቱ ከጀመረበት ግዜ ጀምሮ ሰፊ የስራ ዕድል በመፈጠሩ በቋሚነት ስራ እያገኙ እንደሚኙና በህይወታቸው ላይ ለውጥ ማምጣታቸውን አክለዋል።
በተለይ በኮሪደር ልማቱ በርካታ እውቀቶችን ለመቅሰምና ተጨማሪ የሙያ ባለቤት እንድንሆን አስችሎናል ነው ያሉት።
0 Comments