Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረር ከተማ ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ ለማካሄድ ዝግጅት ተደርጓል-አቶ ጃሚ መሀመድ

በሀረር ከተማ ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ ለማካሄድ ዝግጅት መደረጉን የሀረሪ ክልል ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጃሚ መሀመድ ገለፁ።

አራተኛውን ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ በሀረር ከተማ ሐምሌ 28 እና 29 ለማካሄድ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ የዝግጅት ስራዎች መከናወናቸውን የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ እና የሀረሪ ክልል ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጃሚ መሀመድ ገለፁ።

ግብረ ሀይሉ ለጉባኤው ሲደረጉ የነበሩ ዝግጅቶችን በዛሬው ዕለት ገምግሟል።

የሀረሪ ክልል ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ሀላፊና የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ አቶ ጃሚ መሀመድ እንደገለፁት የሰላም ጉባኤው በሃይማኖት ተቋማት መካከል ያለውን ትስስር ይበልጥ በማጎልበት አበርክቶው የጎላ ነው።

በተለይ ጉባኤው በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ አለመግባባቶችን በመፍታት በአገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚያስችል መሆኑን አክለዋል።

ጉባኤው ችግሮችን በውይይት የመፍታት ልምድን ለማጎልበት የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።

ጉባኤው የሃይማኖት ተቋማትን ይበልጥ በማቀራረብ እርስ በዕርስ የመደጋገፍ ባህልን የሚያጠናክር መሆኑንም አመላክተዋል።

ጉባኤው የሰላም እና አብሮነት ከተማ በሆነችው የሀረር ከተማ መከበሩም ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

በጉባኤው ላይ የፓናል ውይይቶችና ህዝባዊ ኮንፈረንሶች የሚካሄዱ ሲሆን የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች እንደሚሳተፉም ገልፀዋል።

ጉባኤተኞቹ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎም ይጠበቃል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

aoAfaan Oromo