Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረሪ ክልል በ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት ተበረከተ

ሀረር፣መስከረም 9/2017(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል በ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ሌሎች እውቅናና ሽልማት ተበረከተ።

በዕለቱ በ12ኛ ክልፍ ፈተና ከ 5 መቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፣ በማሳለፍ ምጣኔ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ትምህርት ቤቶች የትምህርት አመራሮች እና ከትምህርት ቢሮ በጡረታ የተገለሉ የቀድሞ ሰራተኞች ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ከትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ከሀረሪ ክልል በልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳና ከማኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ ዕጅ ሽልማታቸውን ተረክበዋል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንደገለፁት በሀረሪ ክልል በ12ኛ ክፍል ፈተና እየተመዘገ ያለው አዳጊ ውጤት ክልሉ ለትምህርቱ ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት ማሳያ ነው።

ክልሉ ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ በማሳለፍ ያስመዘገበው ውጤት አበረታች መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ የተመዘገበውን ውጤት ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም ገልፀዋል።

በቀጣዩ የ 2018 የትምህርት ዘመን የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተና በአገር አቀፍ ደረጃ ሙሉ በመሉ ከወረቀት ነፃ በሆነ መልኩ በኦላይን እንደሚሰጥም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በዕውቅናና ሽልማት መርሀ-ግብሩ ላይ የክልሉና ፌዴራል ከፍተኛ የስራ አመራሮች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

aoAfaan Oromo