Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

መስተዳድር ምክር ቤቱ በተከሰተው የዝናብ ዕጥረት ያጋጠመውን የሰብል ጉዳት ለማካካስ እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀመጠ

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በክልሉ በተከሰተው የዝናብ ዕጥረት ያጋጠመውን የሰብል ጉዳት ለአርሶ አደሩ ድጋፍ በማድረግ በቀጣይ የዝናብ ወቅት ለማካካስ እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀመጠ።

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በበልግ እርሻ ስራ እንቅስቃሴ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ሊከሰት የሚችለውን ድርቅ ለመቋቋም ተጠንቶ በቀረበ የመፍትሄ ሀሳብ ላይ መክሯል።

በቀረበው ጥናት መሰረት በክልሉ በዘር መሸፈን የነበረበት መሬት በዝናብ ዕጥረት ምክንያት ሳይሸፈን መቅረቱና በተዘራ ዘር ላይም ውድመት ማጋጠሙ ተጠቁሟል።

በዚህም መሰረት በዝናብ ዕጥረት ያጋጠመውን ጉዳት ለማካካስ ከአካባቢው የአየር ንብረት ጋር ተስማሚ የሆኑ በአጭር ግዜ የሚደርሱ ዘሮችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ አመላክቷል።

በተለይ ከአባቢው ጋር ተስማሚ የሆኑ ቦሎቄ፤ ስንዴ፣ ስኳር ድንች እንዲሁም በኤረርና ሶፊ ወረዳ ቆላማ ቀበሌዎች መጪዉ ግዜ ምቹ የምርት ወቅት ስለሚሆን ማሽላና የመልካሳ የአጭር ጊዜ ዘሮችን በማቅረብ ያሉት ማሳዎች በዘር እንዲሸፈኑ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በሌላ በኩል የከብቶች እልቂትን ቀድሞ ለመከላከል በአንዳንድ አካባቢዎች የተገኝዉን ዝናብ በመጠቀም መኖ በማምረት አርሶ አደሩ ምርቱን በቁጠባ እንዲጠቀም ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁሟል።

ከክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎችን ለመከላከል ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም መስተዳድር ምክር ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

aoAfaan Oromo