Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የብሄራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የዜግችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እያቀለሉ ነው-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

ሀረር፣ነሀሴ 24/2017(ሀክመኮ):-የብሄራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ለዜግች ችግር የመፍትሄ አካል በመሆን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን እያቀለሉ እንደሚገኙ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

በሀረር ከተማ የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ሀገራዊ የልምድ ልውውጥ መድረክ እየተካሄደ ነው።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የልምድ ልውውጥ መድረኩን በንግግ በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት የብሄራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ለዜግች ችግር የመፍትሄ አካል በመሆን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን እያቀለሉ ነው።

የብልፅግና ጉዞ ትውልድን ለቀጣይ ጉዞ ማዘጋጀት ዘመንን ለቀጠይ ትውልድ ማዘጋጀት ነው።

በዚህም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የበጎ ፈቃድ መርሀ-ግብር ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በመገንባት ማህበራዊ መስተጋብሯ የጠነከረ ኢትዮጵያን ለመገንባት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ነው።

በተለይ የዜጎችን የስራ ባህልና አገራዊ የሰላም እሴቶችን በማጎልበት ብሄራዊ መግባባትን እውን እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

የብሄራዊ በጎ ፈቃድ ከራስ በፊት ለማህበረሰብ፣ከኔ እኛን ያስቀደመ፣በእኛ ውስጥ እኔ እጠቀማለው የሚለውን ፍልስፍና በውስጡ የያዘ ከራስ አስቀድሞ ህዝብን ማገልገልን መነሻ ያደረገ መሆኑንም አክለዋል።

በዚህም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የመፍትሄ አካል በመሆን የዜጎችን ችግር እያቀለሉና በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ከፅዳት ጀምሮ በተለያየ መልኩ እያገዙ ነው ብለዋል።

በጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹ በክልሉ በአረንጓዴ አሻራ፣አረጋውያንን በመንከባከብ፣የአቅመ ደካማ ዜጎችን ቤት በማደስና በመገንባት ብሎም ማዕድ በማጋራት እየተሳተፉ እንደሚገኙም ገልፀዋል።

በሚኒስትር ዴኤታ መዓረግ የሰላም ሚኒስትር አማካሪ አቶ ካይዳኪ ገዛሀኝ በበኩላቸው መርሀ-ግብሩ ዘላቂ ሰላም ግንባታና አገራዊ ግንባታ ላይ አገሪቱ የጀመረችውን ጉዞ እያገዘ መሆኑን ገልፀዋል።

የልምድ ልውውጡ በክልሎች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲፈጠር በማስቻል አገልግሎቱን ይበልጥ ለማስፋት መሆኑንም ጠቁመዋል።

የሀረሪ ክልል ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ በበኩላቸው የበጎ ፈቃድ መርሀ-ግብሩ የታለመለትን ማህበራዊ መስተጋብር በማምጣት ውጤት እየተመዘገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር፣የሀረሪ ጉባኤ አፈ-ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ፣የሰላም ሚኒስትር አማካሪ አቶ ካይካዲ ገዛሀኝ፣የክልሉ ከፍተኛ የስራ አመራሮችና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች
የተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አመራሮችና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic