Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ የአስፈፃሚ አካላት የ2018 1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀመረ

ሀረር፣ጥቅምት 11/2018(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል የአስፈፃሚ አካላት የ2018 1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀመረ።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ግምገማውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደጉፁት በ2018 አንደኛው ሩብ ዓመት በሁሉም ዘርፎ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በዛሬው ዕለት የሚካሄደው ግምገማም የአስፈፃሚ ተቋማት የአንዳኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀምን ፈትሾ ለቀጣይ ስራ ለመዘጋጀት የሚያስችል ነው ብለዋል።

ግምገማው በአንደኛው ሩብ ዓመት በተከናወኑ ተግባራት የተስተዋሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ድክመቶችን ለመቅረፍ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይ ተቋማት በሚያከናውኗቸው ተግባራት ማህበረሰቡን ምን ያህል ተጠቃሚ አድርገዋል የሚለው በግምገማው ልዩ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አክለዋል።

ግምገማው ቀጣይ መከናወን በሚገባቸው ተግባራት ላይ አቅጣጫ የሚቀመጥበት እንደሆነም ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic