Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በከተማና ገጠር ፍትሀዊ ልማት እንዲኖር ከምን ግዜውም በላይ ትኩረት ተሰጥቷል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

በከተማና ገጠር ፍትሀዊ ልማት እንዲኖር ከምን ግዜውም በላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

በክልሉ የሚገኙ ብሄር ብሄረሰቦች በብሄር፣እምነት እና የፖለቲካ ልዩነት ሳይለያዩ በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በመደገፋቸው በልማት ስራዎች ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ገልፀዋል።

የክልሉ መንግስት በክልሉ በከተማና ገጠር ፍትሀዊ የመሰረተ ልማት ተደራሽነት እንዲኖር ከምን ግዜውም በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

መንግስት በቀጣዩ የ2018 በጀት ዓመትም በተለይ በገጠሩ ክፍል የኮሪደር ልማት ስራዎችን በሰፊው ለማከናወን በዕቅድ ይዞ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

መሰረታዊ የሆኑ የመሰረተ ልማቶችን ለገጠር ወረዳዎች ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቷል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ከህዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ለማስተካከል የክልሉ መንግስት ከምን ግዜውም በላይ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ህዝብን በብሄር እና ፖለቲካ በመለያየት አንዱን ተጠቃሚ ሌላኛውን ተጎጂ በማስመሰል ህዝብ በመንግስት ላይ ያለውን እምነት ለመሸርሸር የሚንቀሰቀሱ ሀይሎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል።

የነዚህ ሀይሎች ፍላጎት በክልሉ የኮሪደር ልማት አየተመዘገበ የሚኘውን ተጠባጭ ውጤት ማሰናከል በመሆኑ መሰል ሀይሎችን በመታገል የልማት ስራዎችን ማስቀጠል ይገባል።

ፍትሀዊ ያልሆነ ልማት ትርፉ ኪሳራ ነው በመሆኑም ከተማና ገጠሩን አስተሳስሮ በጋራ ለማበልፀግ የክልሉ መንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

መንግስት የጀመራቸው የልማት ስራዎች በታቀደላቸው ጌዜ እውን እንዲሆኑ ማህበረሰቡ አንድነቱን ይበልጥ በማጎልበት የአካባቢውን ሰላም ሊጠበቅ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክር ቤቱ በመጨረሻም ርዕሰ መስተዳድሩ ያቀረቡትና የ2017 በጀት ዓመት ሪፖርትና የ2018 የትኩረት አቅጣጫ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic