Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በበጀት ዓመቱ 139 የአቅመ ደካማ ዜጎች ቤት ግንባታና ዕድሳት ተካሂዷል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

በ2017 በጀት ዓመት በበጎ አድራጎት ተግባራት 1 መቶ 39 ቤቶች ግንባታና ዕድሳት በማካሄድ አቅመ ደካማ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

በተጠናቀቀው የ 2017 በጀት ዓመት አረጋውያን፣አካል ጉዳተኞት፣ደሃና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች ተጠቃሚ በማድረግ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገልፀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ባቀረቡት ሪፖርት በበጀት ዓመቱ ተቋማትና ህብረተሰቡን በማስተባበር 1 መቶ 39 የአቅመ ደካማ ዜጎች ቤት ግንባታና እድሳት መካሄዱን ገልፀዋል።

ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ 43 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው መሆኑን ጠቁመዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ከ 21 ሺ 900 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ከ ከ 27 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የቁሳቁስ ድጋፈና የማዕድ ማጋራት ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።

በተለይ የአረጋውያን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተሰራው ሰራ በሲቪክ ማህበራትና ድርጅቶች ድጋፍና እንክብካቤ የሚያገኙ አረጋውያን ቁጥርን 1 ሺ 355 ማድረስ መቻሉን ጠቁመዋል።

ከክልሉ ተወላጆች በተገኘ ድጋፍ ለ 1 መቶ 96 አካል ጉዳተኞች 1 መቶ 10 ክራንች፣77 ዊልቸርና የትምህርት ቁሳቁስን ጨምሮ ሌሎች ድጋፎች መደረጋቸውንም ገልፀዋል።

ከድህነት ወለል በታች የሆኑ 9 መቶ 22 አካል ጉዳተኞችም መሰረታዊ የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚ ተደርገዋል።

በበጀት ዓመቱ ባጠቃላይ 3 ሺ 171 ዜጎች በከተማና ገጠር የሴፍቲኔት የቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚ የተደረጉ ሲሆን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ 3 መቶ ሴቶችና ህፃናት የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic