Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ማህበረሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

ሀረር፣ጥቅምት 12/2018(ሀክመኮ):-በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ማህበረሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

በሀረሪ ክልል ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የ2018 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቋል።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በግምገማው ማጠቃለያ ላይ እንደገለፁት በክልሉ በ2018 አንደኛው ሩብ ዓመት በሁሉም ዘርፎች አበረታች ስኬቶች ተመዝግበዋል።

በግምገማው በአንደኛው ሩብ ዓመት የነበሩ ጠንከራና ደካማ ጎኖች የተለዩ ሲሆን ውስንነቶችን በመሙላት በሁለኛው ሩብ ዓመት የተሻለ ስኬት ለማስመዝገብ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በክልሉ ቀጣይ አዳጊ የሆነ የኢኮኖሚ እድገት እንዲኖር ርብርብ ማድረግ ይገባል።

በተለይ የግብርና ምርታማነትን ማሳደጉ ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት፣አቅርቦትን በማሳደግ በአምራችና ሸማች መካከል ያለውን ሰንሰለት በማጥበብ፣ የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

ምርት በመደበቅ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳልም ብለዋል።

በሌላ በኩል የገጠር ልማት ስራዎችን በቅንጅት በማከናወን የአርሶ አደሩን ኑሮ የሚያሻሽሉ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ብለዋል።

ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎችን መፍጠርና ኢንቨስትመንቶችን ለክልሉ እና ህዝቡ ካላቸው ጥቅም አንፃር ለይቶ በአግባቡ መምራት እንደሚገባም ጠቁመዋል ።

ወጣቱን በስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባም ገልፀዋል።

በቀጣይም በበጀት ዓመት የተያዙ ፕሮጀክቶችን ስራ ማስጀመር በሂደት ላይ ያሉትን በግዜ በማጠናቀቅ ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ማስቻል እንደሚገበ አክለዋል።

በኮሪደር ልማት ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስፋት ህገ-ወጥ ግንባታና የመሬት ወራራ ላይ ህጋዊ እርምጃ በውሰድ ከተማው በፕላን እንዲመራ ማድረግ ይገባል።

የከተማ ውበት፣የደረቅ ቆሻሻ፣ፍሰሽና የመንገድ መብራትን ዘላቂ በሆነ መልኩ ማስተዳደር ይገባል።

በቀጣም በሁሉም ኢንሼቲቮች አመርቂ ውጤት ለማምጣት ይሰራል በዚህም የወንዝ ዳር ልማት የፍሳሽ ማስወገጃ ስራዎች በትኩረት የሚሰሩ ናቸው ብለዋል።

በማህበራዊ ዘርፉም ብቁ፣ጤናማና ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ሀይል ለማፍራት የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ፣የትምህርት ቤት ምገባን በግዜ ማስጀርና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት መስጠት ይገባል ።

የሴቶች ና አካል ጉዳተኞች ተሳትፍ እንዲኖር ትኩረት ይሰጣል።

በተለይ የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ በማዘመን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ይበልጥ በመቅረፍ የህዝብን ቅሬታ ለመፍታት ይሰራል ብለዋል።

ለዚህም ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በመታገል የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

ሰላምና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የዜጎችን ደህንነት በማረጋገጥ ፍትህን ማስፈን ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራት መሆናቸውንም ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic