ዩኒቨርሲቲው በክረምት በጎ ፈቃድ የአረጋውያን ቤት እድሳት አስጀመረ
የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በሀረር ከተማ የክረምት በጎ ፈቃድ የአረጋውያን ቤት ዕድሳት አስጀመረ።
የአረጋውያን ቤት ዕድሳቱን ያስጀመሩት የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ መሀመድ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢሊባቡር ቡኖ ጋር በመሆን ነው።
ዶ/ር አህመድ መሀመድ የቤት ዕድሳት መርሀ-ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ስራው ጎን ለጎን የዜጎችን ችግር ለማቅለል በማህበራዊ ዘርፎች ላይ ላን ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።
ዩነቨርሲቲው በአለሞ አቀፉ የጁገል ቅርስ ከመቶ ሜትር በላይ መንገድ አልምቶ ማስረከቡን በማስታወስ በክረምት በጎ ፈቃድ ስራም አቅመ ደካማ ዜጎችን በመደገፍ አሻራውን እያኖረ ይገኛል ብለዋል።
የቤት ዕድሳት መርሀ-ግብሩን በአጭር ግዜ በማጠናቀቅ እንደሚያስረክቡም ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም በማህበራዊ ዘርፎች እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢሊባቡር ቡኖ በበኩላቸው ሚኒስቴር መስራያ ቤቱ በቀጣይ በአለም አቀፉ የጁገል ቅርስ መልሶ ልማት በመሳተፍ አሻራውን እንደሚያኖር ገልፀዋል።
በአለም አቀፉ የጁገል ቅርስ በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የተከናወነውን የመልሶ ልማትም ተመልክተዋል።
በመርሃግብሩ ላይ የሀረሪ ክልል ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተገኝተዋል።
0 Comments