Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የ2017 በጀት ዓመት የሀረር ከተማ የማንሰራራት ዘመን የጀመረበት ነው-ርዕሰ መስታድር አቶ ኦርዲን በድሪ

የ2017 በጀት ዓመት በርካታ የልማት ስራዎችን በማከናወን የሀረር ከተማ ለረዥም አመታት ከነበረችበት የቁልቁልት ጉዞ የወጣችበት የማንሰራራት ዘመን መሆኑን የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ፡፡

በተጠናቀቀው የ 2017 በጀት ዓመት የህዝብን ተጠቃሚነት ለሚያረጋግጡ ዘላቂ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ላላቸው ዘርፎች ትኩረት በመስጠት በተሰራው ስራ አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ገልፀዋል፡፡

ከጠቅላላው በጀት 58 በመቶ ድርሻ ለካፒታል ፕሮጀክቶች በመመደብ ወደ ስራ መገባቱን ያስታወሱት ርእሰ መስተዳድሩ አብዛኛው የካፒታል ፕሮጀክቶችን በተሻለ ፍጥነትና ጥራት በአነስተኛ ወጪ በማከናወን ተጨባጭ ለውጥ ተመዝግቧል፡፡

በዚህም በበጀት ዓመቱ 16 የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶችን ግንባታ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ የተቻለ ሲሆን 14 ፕሮጀክቶች በሂደት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

ተግባራዊ በተደረገው የኮሪደር ልማት ስራ የሀረር ከተማን ጽዱ፤ውብ እና ማራኪ በማድረግ ለነዋሪ እና ጎብኚዎች ምቹ ማድረግ መቻሉንም ገልፀዋል፡፡

አዳዲስ የእግረኛና የሳይክል መንገዶች፤የአረንጓዴ ስፍራዎች፤የህዝብ መናፈሻዎች፤የመንገድ መብራቶች፤የፍሳሽ ማስወገጃዎች እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች በኮሪደር ልማት ስራው እንዲሟሉ ተደርጓል ብለዋል፡፡

በከተማው የሚገኙ የህንፃ ግንባታዎችን ስታንዳርድ የማስያዝና የማስዋብ ስራም በልዩ ሁኔታ ትኩረት ተሰጥቶት ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ አክለዋል።

በክልሉ በተከናወኑና በሂደት ላይ በሚገኙ ፕሮጀክቶች በርካታ ዜጎች በተለይ ለወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉንም አክለዋል፡፡

የመሰረተ ልማት ተቋማት ተቀናጅተው እንዲሰሩ በማድረግ በከተማው የኤሌክትሪክ እና የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች በመሬት ውስጥ እንዲዘረጉ መደረጉንም ገልፀዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ስራው የሀረር ከተማን ለረዥም አመታት ከነበረችበት የቁልቁልት ጉዞ ወጥታ የማንሰራራት ጉዞ እንድትጀምር ያስቻለና በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተስፋና ቅቡልነትን በማግኘት በከተማው እድገት የማይፋቅ አሻራ አሳርፏል።

በሌላ በኩል በበጀት ዓመቱ በእቅድ ተይዘው ሲከናወኑ ከነበሩ የህንጻ ግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ 18 ቱን ማጠናቀቅ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ የአርሶ አደሮች ምርት መሸጫ ማእከልና የመሬት ተቋማት ህንጻ ግንባታን ጨምሮ የተጠናቀቁትን የልማት ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ለማስገባት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

ከታለመላቸው አላማ ውጭ ውለው የነበሩ 4 ሼዶች ወደ መንግስት ይዞታ ተመልሰው አስፈላጊው የጥገናና እድሳት የተደረገላቸው ሲሆን ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

በአጠቃላይ በ2017 በጀት ዓመት ለማከናወን በእቅድ የተያዙ ፕሮጀክቶች አማካይ የፊዚካል አፈፃፀም 92 በመቶ ሲሆን አዝጋሚ የሆኑ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ግዜ እንዲጠናቀቁ አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ እየተደገረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic