Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የኮሪደር ልማት ስራ ለአምራች ኢንዱስትሪው የስራ መነቃቃት ፈጥሯል-የሀረሪ ክልል ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

ሀረር፣ነሀሴ 17/2017(ሀክመኮ):-የኮሪደር ልማት ስራ ለአምራች ኢንዱስትሪው የስራ መነቃቃት መፍጠሩን የሀረሪ ክልል ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ እስማኢል ዩሱፍ ገለፁ።

በሀረሪ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ የኢኮኖሚ መነቃቃት እየፈጠረ እንደሚገኝ የሀረሪ ክልል ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ እስማኢል ዩሱፍ ገለፁ።

የኮሪደር ልማት ስራውን በአካባቢ የሚገኙ ፀጋዎችን ተጠቅሞ በማከናወን የውጭ ምንዛሬን ለማስቀረት እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በክልሉ የተቋቋመው ማስ ኢንጅነሪንግ የብረታ ብረት ፋብሪካም ለኮሪደር ልማቱ የሚውሉ ግብዓቶችን በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በተለይ መብራትና ምሰሶ የመሳሰሉትን የውጭ አገር ምርቶች በአገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሬን በማስቀረት በአነስተኛ ወጪ ከተማዋን ማስዋብ መቻሉን አክለዋል።

ፋብሪካው የስራ አድማሱን በማስፋት ከሀረሪ ክልል ባሻገር በአጎራባች ከተሞች እየተከናወኑ ለሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ግብዓት እያቀረበ ይገኛል።

መንግስት የውጭ አገር ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የሰጠው ትኩረት በክልሉ ለሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች የስራ መነቃቃት የፈጠረ መሆኑን ነው አቶ እስሚኢል ዩሱፍ የገለፁት።

በዚህም ኢንዱስትሪዎቹ አቅማቸውን በማጎልበት ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠራቸውን እና ዘርፉ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ስኬት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ እያስቻለ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በቀጣይም የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ይበልጥ በማጎልበት ዘርፉ ማመንጨት የሚገባውን ኢኮኖሚ እንዲያመነጭ ለማስቻል ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።

በማስ ኢንጅነሪን የብረታ ብረት ፋብሪካ አግኝተን ያነጋገርናቸው ወጣቶች በበኩላቸው ባገኙት የስራ ዕድል የኢከኖሚ ተጠቃሚ እየሆኑ እምደሚገኙ ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic