Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የክልላችንን ቅርስ፣ ባህል እና ታሪክ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በመደመር ማስቀጠል ይገባል – አቶ ኦርዲን በድሪ

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የክልላችንን የዳበረ ቅርስ፣ ባህል እና ታሪክ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በመደመር ማስቀጠል ይገባል አሉ።

‘ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ’ በሚል መሪ ቃል ጳጉሜን 5 የነገው ቀንን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት፤ መጪው ጊዜ ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ውጭ አይታሰብም ብለዋል።

መሪ ቃሉ የቀጣይ ልማታችን መሣሪያ፣ የወደፊታችን መንገድ እና የህዝባችን አቅም ማዘመኛ እንደሆነ የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዋል።

ከመጻኢ ብሩህ ራዕይ፣ አዎንታዊ ለውጥ፣ እድገት፣ ከብሩህ ተስፋ እና ጊዜ አንፃር የሚገለጽ እንደሆነ አንስተው፤ የወደፊቱን አዎንታዊ ዕይታ፣ መነሳሳት እና የተሻለ ጊዜን የሚያመላክት ነው ብለዋል።

ዕለቱን ስናከብር የክልላችንን የዳበረ ቅርስ፣ ባህል እና ታሪክ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በመደመር፤ የህዝባችን ተጠቃሚነት አጠናክረን ለማስቀጠል ያለንን ዝግጁነት በማረጋገጥ ይሆናል ነው ያሉት።

በክልሉ የዲጂታል መሠረተ ልማት በማጠናከር፣ የህዝብ አገልግሎቶችን ዲጂታል በማድረግ እና ለወጣቶች የቴክኖሎጂ ክህሎት ስልጠናዎችን በስፋት ለማዳረስ ትኩረት እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።

መጪው ዓመት በዲጂታል ፈጠራ ታግዘን የነገውን የጋራ ራዕይ የምናሳካበት ጊዜ ልናደርገው ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic