Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው ለሁለት ቀናት በሚኖረው ቆይታ የክልሉ መንግስት የ2017 የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 እቅድ በርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበት እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።

እንዲሁም የክልሉ የዋና ኦዲተር መ/ቤት እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2017 እቅድ አፈፃፀምና የ2018 በጀት አመት ሪፖርትና እቅድን በማድመጥ በቀረበው ሪፖርት እና እቅድ ላይ በመወያየት እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ የክልሉ መስተዳድር የ2018 ዓ.ም የሥራ ዘመን ማስፈጸሚያ ረቂቅ በጀት ላይ በመምከርም ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚኖረው ቆይታ የተለያዩ ሹመቶችን ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

በዛሬው ዕለት መካሄድ በጀመረው ጉባዔ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፣የክልሉ ምክር ቤት አባላት፣የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic