Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የሐረሪ ክልል የልማት ሥራዎች ሀገራዊ ግቦችን የማሳካት ትግበራ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን ያሳያሉ – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

በሐረሪ ክልል እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ሀገራዊ ግቦችን የማሳካት ትግበራው ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ለመሸጋገሩ አብነቶች ናቸው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት በሐረሪ ክልል በስራ ላይ የሚገኙ ማስ ኢንጅነሪንግ ኢንተርፕራይዝና አዱ የዱቄት ፋብሪካን መጎብኘታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

የብረታ ብረት ፋብሪካው በከተማ እንዲሁም በአጎራባች ከተሞች እየተሰሩ ለሚገኙ የኮሪደር ልማት እና የከተማ ማስዋብ ስራዎች ትልቅ ሚናን እየተወጣ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የዱቄት ፋብሪካውም የስንዴና የቦቆሎ ዱቄትን በማምረት በጅምላና በችርቻሮ ለሕዝቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማከፋፈል ላይ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

በሌላ በኩል የእንቁላልና የወተት መንደርን እንደተመለከቱ ጠቁመው ÷ ሥራዎቹ የሌማት ትሩፋት በምግብ ራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት ሚናው ላቅ ያለ ስለመሆኑ ማሳያዎች ናቸው ብለዋል፡፡

በሐረሪ ክልል እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ሀገራዊ ግቦችን የማሳካት ትግበራው ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ለመሸጋገሩ አብነቶች ናቸው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic