Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የህዳሴ ግድቡ ግንባታ በስኬት ተጠናቆ ለምርቃት መብቃቱ ለኢትዮጵያ የመንሳራራት ዘመን ማሳያ ነው-ምክትል አፈ-ጉባኤ አሚና አብዱልከሪም

ሀረር፣ጷግሜ፣4/2017(ሀክመኮ):-የህዳሴ ግድቡ ግንባታ በስኬት ተጠናቆ ለምርቃት መብቃቱ ለኢትዮጵያ የመንሳራራት ዘመን ማሳያ መሆኑን የሀረሪ ብሄራዊ ጉባኤ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም ገለፁ።

በሀረሪ ክልል የመንሰራራት ቀን “ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከብሯል

ዕለቱ በልማት ስራዎች ጉብኝት እና የአባይ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ በኑር ፕላዛ ላይ በመሰባሰብ ለግድቡ ድጋፍ በማሳየት ነው የተከበረው።

የሀረሪ ብሄራዊ ጉባኤ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም እንደገለፁት በመንሰራራት ቀን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ መከናወኑ እጥፍ ደስታ የተገኘበት ነው።

የህዳሴ ግድቡ ግንባታ በስኬት ተጠናቆ ለምርቃት መብቃቱ ለኢትዮጵያ የመንሳራራት ዘመን ማሳያ ነው።

ግድቡ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ውጤት፣ የህብረ ብሄራዊነት መገለጫና የአገር ኩራት ነው ብለዋል።

በህዳሴ ግድቡ የተገኘውን ድል በሁሉም የልማት ዘርፎች አጠናክሮ በማስጠል የኢትዮጵያን የብልፀግና ጉዞ ለማፋጠን እንደሚሰራም ገልፀዋል።

ለአገር የሚከፈል መስዋዕትነት ፍሬው ጣፋጨ ነው ያሉት ምክትል አፈ-ጉባኤዋ በሀረር ከተማ በኮሪደር ልማት የተገኘው ውጤት ሌላኛው የሀረሪ ክልል የመንሰራራት ዘመን ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስትና ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ የክልሉ የከተማና ገጠር ወረዳዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic