የሀረሪ ብሄራዊ ጉባኤ ሲያካሂደው የነበረው 6ተኛ ዙር 4ኛ አመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ
የሀረሪ ብሄራዊ ጉባኤ ሲያካሂደው የነበረው 6ተኛ ዙር 4ኛ አመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የቀጣይ ግዜ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቀቀ።
ጉባኤው የሀረሪ ጉባኤ፣የክልሉ ትምህርት ቢሮ እና የባህል ቅርስና የቱሪዝም ቢሮ የ2017 የስራ አፈፃፀምን በመገምገም ሪፖርቱን ብሎም የ2018 ዕቅድን አፅድቋል።
በመጨረሻም የቀጣይ ግዜ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ጉባኤው ተጠናቋል።
በጉባኤው ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣የሀረሪ ጉባኤ አፈ-ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ፣የሀረሪ ጉባኤ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪምን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና መራጮች ተገኝተዋል።
0 Comments