Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በአብሮነት እና በአንድነት ማሸነፍ እንደሚቻል በተግባር የታየበት ነው

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በአብሮነት እና በአንድነት ማሸነፍ እንደሚቻል በተግባር የታየበት ነው ሲሉ የሐረር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

አስተያየት ሰጪዎቹ እንዳሉት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ለምረቃ በመብቃቱ እጅግ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል።

የግድቡ ግንባታ የእኛነታችን መገለጫ እና በአንድነትና በአብሮነት ማሸነፍ እንደምንችል ያሳየንበት ነው ብለዋል።

በእኛ ትውልድ ያየነው ትልቁ የጀግንነት ምልክት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ግድቡ ምረቃ በመብቃቱ እጅግ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል።

የግድቡ ለምረቃ መብቃት ለቀጣይ ስራዎቻችን በአብሮነትና በጀግንነት እንድናስቀጥል መነሳሳትን ፈጥሯል ብለዋል።

ታላቁ የኢትዮዽያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የዘመናችንና የሀገራችን ትልቁ ፕሮጀክትና ድል ነው፤ እንደብሔራዊ ድላችንም እያከበርን ነው ብለዋል አስተያየት ሰጪዎቹ።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአብሮነት እና በአንድነት ማሸነፍ እንደሚቻል በተግባር ያሳየንበትና ቀጣዩ ትውልድም በተባበረ ክንድ ለመስራት ማነሳሳትን የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮዽያውያን የተባበረ ክንድ የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለምረቃ በመብቃቱ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic