Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በ2018 በጀት ዓመት የትምህርት ጥራትን ይበልጥ ለማጎልበት ይሰራል-አቶ ጌቱ ነገዎ

በ2018 በጀት ዓመት የትምህርት ጥራትን ይበልጥ በማጎልበት የተማሪ ውጤትን ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ በቀጣዩ የ2018 በጀት ዓመት በትምህርት ዘርፍ ልዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ከትምህርት ዘርፉ አመራሮች ጋር መክሯል።

የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ እንደገለፁት በቀጣዩ 2018 በጀት ዓመት የትምህርት ጥራትን ይበልጥ በማጎልበት የተማሪ ውጤትን ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል።

ዘርፉን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የትምህርት ዘርፉን ሪፎርም ከማድረግ ጀምሮ የመምህራንና ትምህርት አመራሮችን አቅም ለማጎልበት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ገልፀዋል።

በተለይ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ብሎም በግብዓት እንዲደራጁ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በትምህርት ቤቶች የተጀመሩ የተማሪ ምገባ መርሀ-ግብርን በማጎልበት የተማሪዎች ከትምህርት ቤት የመቅረት ምጣኔን በመቀነስ የትምህርት ቅበላ አቅምን ለማሳደግም ይሰራል ብለዋል።

በሌላ በኩል በግል ትምህርት ቤቶች ከማህበረሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለማረም አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ ለማረም እንደሚሰራ አክለዋል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ መምህራን፣ሴት ርዕሰ መምህራንና በጡረታ ለተገለሉ መምህራን የእውቅናና ሽልማት መርሀ-ግብር ተካሂዷል።

የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ዘከሪያ አብዱልአዚዝ እንደገለፁት በጉብዝናቸው ወራት በሞያቸው አገራቸውን ያገለገሉ መምህራንን ማገዝና መደገፍ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በቀጣይም መሰል የእውቅናና ድጋፍ መርሀ-ግብሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ ከትምህርት ዘርፉ ባለ ድርሻ አካላት ጋር የዕቅድ ርክክብም ተደርጓል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic