በክልሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች በተሻለ ፍጥነት ተጠናክረው ቀጥለዋል-አቶ ኦርዲን በድሪ
ሀረር ጥር 10/2017(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል የኮሪደር ልማት ስራዎች በተሻለ ፍጥነት ተጠናክረው መቀጠላቸውን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተዳዶሩ በመስክ ምልከታው የኮሪደር ልማት ስራው በተሻለ ፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በተለይ በከተማው በ1.3 ሄክታር መሬት ላይ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የአባድር ፕላዛ በተሻለ ፍጥነት እየተከናወነ ሲሆን የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ከግንባታው ስራ ጎን ለጎን እየተካሄዱ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
የአባድር ፕላዛ አካባቢውን ባማከለ መልኩ ከአለም አቀፉ የጁገል ቅርስ ጋር በማስተሳሰር እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን የቱሪዝም ፍሰቱ እንዲጨምር በማድረግ ፋይዳው የጎላ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በቀጣይም በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው አመራሩ የራሱን ሚና ሊጫወት እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

0 Comments