Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ የሆቴሎች እና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አሰሪዎች ማህበር ተመሰረተ 

ሐረር፤ሚያዝያ 2/2017(ሐክመኮ):-በሐረሪ ክልል የሆቴል እና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አሰሪዎች ማህበር ተመሰረተ።

በማህበሩ ምስረታ ላይ የሐረሪ ክልል ባህልና ቅርስ ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ እንደገለፁት የማህበሩ መመስረት ለክልሉ ቱሪዝም ዘርፍ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦው ያበረክታል።

በተለይ የሆቴሎች መስተንግዶ አገልግሎት ጥራትን ከፍ በማድረግ የክልሉን ባህላዊ፤ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ መስቦችን ለአለም ለማስተዋወቅ የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ጉልህ አበርክቶ ይኖረዋል።

ማህበሩ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ግዴታቸውን እንዲወጡ እና መብታቸውን ለማስከበር ብሎም በዘርፉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ከመንግስት ጋር በቅርበት በመስራት ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል።

ማህበሩን መመስረት ያስፈለገው ማህበሩ ህጋዊ ሰውነት ኖሮት እውቅና እንዲያገኝና መብቱ የተጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል መሆኑን የገለፁት ደግሞ የማህበሩ ተወካይ አቶ አለማየሁ ድንቁ ናቸው።

ማህበሩ ህጋዊ መሠረትን ይዞ መንቀሳቀስ እንዲችልና ዘርፉ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት እንዲወጣ የክልሉ ባህልና ቅርስ ቱሪዝም ቢሮ ድጋፍ እንደሚያስፈልገውም ገልፀዋል።

በምስረታ መርሀ ግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ አመራሮች፣የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አሰሪዎች፤ባለቤቶችና ተወካዮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic