Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ በ2017 ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የተሰሩ ስራዎች ውጤት ማስገኘታቸው ተገለጸ።

በሀረሪ ክልል በ2017 ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የተሰሩ ስራዎች ውጤት ማስገኘታቸው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ኡመር ገልጸዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሮዛ ኡመር በቢሮው በ2017 በተከናወኑ ተግባራት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በክልሉ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የኑሮ ውድነቱን ለማርገብ የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራ ነበር ብለዋል።

በዚህም ምርትና ምርታማነት የማሳደግና አምራቹና ሸማቹን የማገናኘት ስራ በትኩረት መሰራቱን ጠቁመዋል።

በክልሉ የሚገኘውን ውስን መሬት በአግባቡ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ርብርብ ሲደረግ መቆየቱን አንስተዋል።

በከተማ ግብርና እና በሌማት ትሩፋት እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች እንዲጎለብቱ የመደገፍ ስራ ሲሰራ መቆየተን ጠቁመው የዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚነት የማጎልበት ስራም መሰራቱን ገልጸዋል።

በተለይ በሌማት ትሩፋት የመኖ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ የመኖ ማቀነባባሪያ ማሽን በመትከል ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ ነው።

እንዲሁም የተለያዩ የአትክልት ዘሮችን፣ የውሃ ማጠራቀሚያ ሸራ እና የውሃ መሳቢያ ሞተሮችን ለአርሶ አደሮች ማሰራጨት መቻሉን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የብርዕና የአገዳ ሰብሎችን ፣የጥራጥሬ እና የቅባት ሰብሎችን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ረገድም ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

በተለይም የወተት፣ ዕንቁላል፣ ስጋ ፣የማር ምርት ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰራው ስራ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በአትክልት፣ በቡና እንዲሁም በእንሰሳት ተዋፅኦ ላይ የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ ምርታማነትን ለማሳደግም ሲሰራ እንደነበር ገልጸዋል።

እንዲሁም በመኸር 475 ሄክታር መሬት በስንዴ መሸፈኑን ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም 9 የህብረት ስራ ማህበራትን ለማደራጀት ታቅዶ 12 ማህበራትን ማደራጀት መቻሉን ገልጸዋል።

በያዝነው የበጀት አመትም የክልሉ መንግስት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማጎልበት የሚያከናውናቸው ሌሎች ተግባራት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic