በክልሉ በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት አበረታች ውጤት ተመዝግቧል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ
በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
በተጠናቀቀው የ 2017 በጀት ዓመት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ገልፀዋል።
ትምህርት ቤቶችን በግብዓት በማደራጀት፣ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በማሳደግ ተማሪዎች ተገቢውን ክህሎትና እውቀት እንዲጨብጡ ለማስቻል ትኩረት ተሰጠሰቶ ሲሰራ ቆይቷል።
የትምህርት ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ በተቀረፀው ስትራቴጂ መሰረት በከተማና ገጠር ብሎም በሴትና ወንድ ተማሪዎች መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ በትኩረት እየተሰራ ነው።
የክልሉ መንግስት ከ 40 ሚሊየን ብር በላይ በመመደብ በ በክልሉ በሚገኙ 67 ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ምገባ በማካሄድ ከ 38 ሺ በላይ ተማሪዎች ተጠቃሚ አድርጓል።
በዚህም የተማሪዎች መጠነ ማቋረጥ ና ማርፈድ ምጣኔን ዝቅ በማድረግ የተማሪዎች የቅበላ አቅምን ማሳደግ መቻሉን አክለዋል።
የምገባውን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ማህበረሰቡን በትምህርት ቤት ምገባ በማሳተፍ ከ1.8 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰብ መቻሉንም ጠቁመዋል።
በቀጣይም በተለይ በገጠር ወረዳዎች የተማሪዎች መጠነ ማቋረጥን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት በትኩረት ይሰራል።
በሌላ በኩል የመምህራን አቅምን ለመገንባት የተለያዩ ስልጠናዎች እንዲወሰዱ የተደረገ ሲሆን በዚህም የተማሪዎች የማለፍ ምጣኔን ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል።
በቀጣይም የመምህራ አቅምን በማጎልበት የትምህርት ጥራትን እና የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሳደግ ይሰራል።
በበጀት ዓመቱ 6 አፀደ ህፃናት ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል፣ በገጠር ወረዳዎች የተገነቡ ኦ ክፍሎች በግብዓት እንዲደራጁ ተደርጓል።
እያደገ ከመጣው የተማሪ ቁጥር አንፃር በተለይ በአዲሱ ስርዓ ትምህርት ለተጀመሩ አዳዲስ ትምህርቶች መምህራን የሟሟላት ስራ ተከናውኗል።
የመምህር እጥረት ባለባቸው የትምህርት ዓይነቶች የተስተዋለውን ውስንነት ለመሙላት እጩ መምህራንን በመመልመል ሀረር መምህራን ኮሌጅ ገብተው እንዲሰለጥኑ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
የተማሪ መፅሀፍ ምጣኔን በተመለከተ በአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከተወሰኑ መፅሀፍት በስተቀር 1 ለ 1 ማድረስ የተቻለ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪ መፅሀፍ ምጣኔን 1ለ 1 ማድረስ ተችሏል።
የተማሪ መፅሀፍ ማሳተሚያ ዋጋ መናሩን ተከትሎ የግል ትምህርት ቤቶች የመፅሀፉን አንድ አራተኛ ዋጋ ብቻ በመክፈል ቀሪውን በብድር በመውሰድ ለተማሪዎች ተደራሽ እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል።
በተጠናቀቀው የ 2017 የትምህርት ዓመት በክልሉ ባጠቃላይ ከ 88 ሺ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር የተቻለ ሲሆን ከታቀደው አንፃር 97 በመቶ የትምህርት ተደራሽነትን ማረጋገጥ ተችሏል።
ከ 3 ሺ 400 በላይ ልዩ ፍላጎት ያላቸውና ድጋፍ የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መቻሉንም አክለዋል።
የተማሪዎች የማለፍ ምጣኔን ለማሳደግ የቢሮ ዓመራሮችን በትምህርት ቤቶች በመመደብ በተለይ የ6ተኛ፣8ተኛና 12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲወስዱ ከማድረግ ጀምሮ አስፈላጊው የደጋፍና ክትትል ስራ ተከናውኗል።
በክልሉ የ6ተኛ፣8ተኛና 12ኛ ክፍል ፈተና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ የተሰጠ ሲሆን የተሻለ ውጤት ይመዘገባል ተብሎ እንደሚጠበቅም አክለዋል።
በግል ትምህርት ቤቶች ላይ በተደረገ ቁጥጥርም አንድ ከደረጃ በታች የሆነ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህረት ቤት እንዲዘጋ መደረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ ባቀረቡት ሪፖርት ገልፀዋል።
0 Comments