Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀኪም ጋራ ላይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ ለማከናወን ይሰራል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

በሀኪም ጋራ ላይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ በማከናወን ተራራውን ወደ ፓርክነት ለመቀየር እንደሚሰራ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በክልሉ የሚገኘው የሀኪም ጋራ ላይ የመስክ ምልከታ አድርጓል።

በወቅቱም ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት ተራራውን በህግ እና ስርዓት በማስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ስራ ለማከናወን በትኩረት ይሰራል።

በአካባቢው የሚስተዋለውን ህገ-ወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ ስርዓት በማስያዝ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ በሚያስችል መልኩ ለማልማት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በተለይ በአካባቢው የተሽከርካሪና እግረኛ መንገድን ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶችን በማሟላት ተራራውን ይበልጠ አረንጋዴ በማድረግ፣ወደ ፓርክ የመቀየር ስራ እንደሚሰራ ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ያመላከቱት።

በቀጣይም ህገ-ወጥ ግንባታን ከመከላከል ባሻገር በጥናት ላይ በመመሰረተ ህጋዊ መሆን የሚገባቸውን ህጋዊ በማድረግ የህግ ማስከበር ስራ እንደሚሰራም ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic