Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረሪ ክልል የብልፅግና ፓርቲ 5ተኛ አመት ምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ መሰረታዊ ፓርቲ አባላት የልማት ስራዎችን ጎበኙ

በሀረሪ ክልል የብልፅግና ፓርቲ 5ተኛ አመት ምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ መሰረታዊ ፓርቲ አባላት በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ ፓርቲው ባለፍት አምስት አመታት ያከናወናቸውን የሌማት ትሩፋቶች ጨምሮ በክልሉ እየተሰሩ የሚገኙ ኮሪደር ልማቶች የጁገል አለም አቀፍ ቅርስ ማስዋብ ስራዎችን ተመልክተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ በድሬ ጠያራ ወረዳ በሱቁል ቀበሌ የተገነባው የመስኖ ግድብ በእለቱ ከተጎበኙት መካከል ነው።

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ” በህብር ወደ ኢትዮጽያ ልዕልና ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ያለው የፓርቲው 5ተኛ አመት የምስረታ በአል በቀጣይም በተለያዩ ሁነቶች መከበሩን እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic