Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረሪ ክልል አምስቱን የጳጉሜ ቀናት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል- ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

በሀረሪ ክልል አምስቱን የጳጉሜ ቀናት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ

ርዕሰ መስተዳደሩ በሰጡት መግለጫ በክልሉ አምስቱ የጳጉሜን ቀናት በተሰጣቸው ስያሜና ተግባር መሰረት በተለያዩ መርሃግብሮች ለማክበር የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

እየተገባደደ ያለው አመት እንደ ሀገር አዳዲስ ስኬቶች የተመዘገቡበት አመት መሆኑን ጠቁመው በክልሉ በተሰሩ በርካታ ስራዎችና በተመዘገቡ ስኬቶች የማንሰራራት ዘመን ጅማሮ የታየበት መሆኑን ጠቁመዋል።

መጪውን አዲስ አመት ስንቀበልም ለስኬት ያበቁንን ተሞክሮዎች በማጉላትና በማስጠል ለተጨማሪ ድሎች መነሳሳት የሚያስችሉ መደላድሎችን በሚፈጥር መልኩ ነው ብለዋል፡፡

የጳጉሜ ቀናት መርሃግብር ዋና ዓላማ ሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎች እና እየታዩ የሚገኙ ፈጣን ለውጦች ለማስቀጠልና ህብረተሰቡም በልማቱ ላይ የሚያደርገውን ንቁ ተሳትፎ ለማጎልበት ያለመ ነው።

በክልሉም አምስቱን የጳጉሜ ቀናት “እመርታና ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በክልሉ በተለያዩ መርሃግብሮች ይከበራል ብለዋል።

በመሆኑም በ2017 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት የተለያዩ ስያሜዎች እንደተሰጣቸው ጠቅሰው፤ በዚህም ጳጉሜን 1 የጽናት ቀን፤ ጳጉሜን 2 የህብር ቀን፤ ጳጉሜን 3 የእምርታ ቀን፤ ጳጉሜን 4 የማንሰራራት ቀን እና ጳጉሜን 5 የነገው ቀን በሚል እንደሚከበሩ ነው የገለፁት።

ቀናቱ እንደየተሰጣቸው ስያሜና ተግባር መሰረት በተለያዩ መርሃግብሮች ይከበራሉ ብለዋል።

አምስቱ የጳጉሜ ቀናት የሚከናወኑ መርሃግብሮች የተሳኩ እንዲሆኑ ሁሉም የመንግስት ተቋማት፣ በየደረጃ የሚገኝ አመራር፣ የመንግስት ሠራተኞችና መላው ሕዝቡ የሚጠበቅበትን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic