Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረሪ ክልል በ2017 በጀት አመት በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ

በሀረሪ ክልል በ2017 በጀት አመት በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ በተቋሙ በ2017 በጀት አመት የተከናወኑ ስራዎችን በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ በመግለጫቸው በ2017 በጀት አመት በክልሉ በኮሙዩኒኬሽን እና በሚዲያው ዘርፍ አመርቂ ስራዎች ተከናውነዋል  ብለዋል።

በዚህም ልማትና ሰላም እንዲጠናከር መልካም እሴቶች እንዲጎለብቱ እና ህዝቡ በክልሉ በሚከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የሚያደርገውን ተሳትፎ ማሳደግ ያስቻሉ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል።

በዋናነትም በክልሉ የሚከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን የማህበራዊ ሚዲያና የክልልና ሀገር አቀፍ ሚዲያዎችን በመጠቀም ለህዝቡ ተደራሽ ተደርጓል ብለዋል።

በተለይም በክልሉ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን እንዲተዋወቁ እንዲሁም የክልሉ ህዝብ በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት የመኖር እሴቶች እንዲጠናከር በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች የተጠናከረ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል።

መረጃን ለማህበረሰቡ ከማድረስ ባለፈ የአፍራሽ ሀይሉን አጀንዳ በማምከን ረገድ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በተለይም የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ስራን በአግባቡ መምራትና ወቅቱን የዋጀ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ተግባራትን ማከናውን መቻሉን ተናግረዋል።

ኃላፊው አክለውም የክልሉን መልካም ገፅታ በመገንባት በህዝብና በመንግስት መካከል ሁነኛ የመረጃ ድልድይ ሆኖ ተግባቦትን የመፍጠር ስራዎችም ሲከናወኑ መቆየቱን አክለው ገልፀዋል። 

በተለይም በክልላዊና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንዲያጎለብት ለማስቻል ትኩረት ተሰጥቶት ስለመሰራቱ አንስተው በሀገራዊ ጉዳዮች ላይም የጋራ መግባባት ከመፍጠር አንጻር የኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ የድርሻውን እንዲወጣ ለማስቻል ጥረት መደረጉን አስረድተዋል።

በ2018 የበጀት አመትም ተቋሙ የተቋቋመለትን ዓላማ በብቃት ለመወጣትና የህብረተሰቡን የመረጃ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic