Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በሀረር ከተማ በ 96 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባውን ሪጅናል ላብራቶሪ መርቀው ከፈቱ

ሀረር፣ነሀሴ 7/2017(ሀክመኮ):-የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በሀረር ከተማ በ 96 ሚሊየን በር የተገነባውን ባለ 3 ወለል ሪጅናል ላብራቶሪ ከጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር በመሆን መርቀው ከፍተዋል።

በሀረር ከተማ በ 96 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ባለ 3 ወለል ሪጅናል ላብራቶሪ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደረገ ።

ሪጅናል ላብራቶሪውን መርቀው የከፈቱት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ከጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር በመሆን ነው።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ላብራቶሪውን መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት ከለውጡ ወዲህ በጤና ዘርፉ ያጋጠሙ ስብራቶችን ለመጠገን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል።

በተለይ የጤና ዘርፉን አገልግሎት ይበልጥ በማጎልበት አገሪቱን ወደ ብልፅግና በማሻገር ማህበራዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ለጤናው ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ በተሰራው ስራ በሽታን በመከላከልና አክሞ በማዳን አበረታች ውጤት ተመዝግቧል።

መንግስት ለሰላምና ጤና ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት የዜጎችን ህይወት ለማሻሻል እንደሚሰራ በመጠቆም ላብራቶሪው የጤና አገሌግሎቱን በተሻለ ደረጃ ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።

በተለይ ዜጎች መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን በአካባቢያቸው እንዲያገኙ በማስቻል የሀረር ከተማን የጤና ቱሪዝም ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ነው።

በቀጣይም ላቦራቶሪውን በአስፈላጊው ግብዓትና የሰው ሀይል በማደራጀት ለዜጎች ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው ከለውጡ ወዲህ የጤና ፖሊሲውን ማሻሻል በሽታን በመከላከልና አክሞ ለማዳን በተሰራው ስራ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

መንግስት ለጤና መሰረተ ልማት ተደራሽነት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራነው መሰል ላቦራቶሪዎች መገንባታቸው ለዘርፉ ለተሰጠው ትኩረት ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።

ላብራቶሪው አለም አቀፍ እስታንዳርድን በሚያሟላ መልኩ በውስጡ የታካሚ መቆያ የናሙና መሰብሰቢያና ሌሎች አገልግሎቶችን አካቶ መገንባቱንም አመላክተዋል።

የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር አብዲ አሚን በበኩላቸው ላቦራቶሪው የጤናውን ዘርፍ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

በማዕከሉ የፎረንሲክ ምርመራ ለመጀመርም በዕቅድ ተይዞ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በምርቃት መርሃግብር ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፣ የሀረሪ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሮዛ ኡመር ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ፣የፌደራልና የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic