Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

“ማረሚያ ቤቱ ታራሚዎች በስነ ምግባርና ሙያ ታንፀው የሚወጡበት እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቷል-ኮሚሽነር አድናን አህመድ

“ማረሚያ ቤቱ ታራሚዎችን በሙያና ስነ ምግባር በማነፅ ብቁ ዜጎች የሚፈጠሩበት እንዲሆን ትኩረት መሰጠቱን የሀረሪ ክልል ማረሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድናን አህመድ ገለፁ።

ኮሚሽነሩ የኮሚሽኑን የቀጣይ ግዜ አቅጣጫ በማስመልከት በሰጡት መግለጫ የታራሚዎችን ሰብዓዊ መብት በመጠበቅ የተመዘገበውን ውጤት በ 2018 ለማጎልበት ይሰራል ብለዋል።

በተለይ ታራሚዎችን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች እንዲሰለጥኑ በማስቻል የተመዘገበውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራ ነው የገለፁት።

ታራሚዎች በማረሚያ ቆይታቸው የባህሪ ለውጥ እንዲያመጡ በማስቻል ወንጀልን የሚፀየፉ ዜጎች እንዲሆኑ ለማስቻል በትኩረት ይሰራል።

ኮሚሽኑ ታራሚዎች የእርምት ግዜያቸውን አጠናቀው ከማህበረሰቡ ጋር በሚቀላቀሉበት ግዜ በሰለጡኑበት የሙያ ዘርፍ በመሰማራት ሰላማዊና አምራች ሀይል በመሆን ገበያውን እንዲቀላቀሉ ማስቻል አላማው አድርጎ እየሰራ ነው።

በዚህም የማረሚያ ቤቱን የማረም ማነጽ ስርዓት ይበልጥ በማሻሻል ታራሚዎች በስነ ምግባርና ሙያ ታንፀው እንዲወጡ ለማስቻል ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ሲሉ ገልፀዋል።

በዚህም በአዲሱ የ 2018 በጀት ዓመት ታራሚዎችን ገበያ ላይ በሚፈለጉ የሙያ ዘርፎች ይበልጥ ለማብቃት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አክለዋል።

ማረሚያ ኮሚሽኑ የሕግ ታራሚዎችን የማረምና ማነጽ ስርዓቱን ይበልጥ በማሻሻል የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ኮሚሽነር አድናን አህመድ የገለፁት።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic