Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

“ለብሔራዊ ጥቅም መረጋገጥ ኢትዮጵያዊ አንድነትን ማረጋገጥ ቁልፍ ጉዳይ ነው” አቶ ጌቱ ወዬሳ

“ለብሔራዊ ጥቅም መረጋገጥ ኢትዮጵያዊ አንድነትን ማረጋገጥ ቁልፍ ጉዳይ ነው” ሲሉ የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።

በሀረሪ ክልል ከህዝብ ግንኙኑትና ኮሙዩኒኬሽን ባለሞያዎች ጋር “ብሄራዊ ጥምቅ እና ጂኦ ስትራቴጂክ ቁመና” ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ እንዳሉት የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር የህልውና ጉዳይ ነው።

የአገራችን ብሄራዊ ጥቅም በማስከበሩ ሂደት የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሚና ከፍተኛ ነው።

በመሆኑም መንግስት የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅ የሀገርን ሕልውና፣ ደኅንነትና፣ ብልጽግና አቅምን በማጎልበት ኢትዮጵያን ተፅኖ ፈጣሪ አገር ለማድረግ የጀመራቸውን ስራዎች ማገዝና መደገፍ እንደሚገባ ገልፀዋልጸ።

በተለይ አሰባሳቢ ትርክቶች የበላይነትን እንዲይዙ በማድረግ በአገሪቱ የጋራ መግባባት እንዲፈጠረ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በዚህም የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ ብሄራዊ ጥቅምን በተመለከተ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በማስጨበጥ ሀገራዊ አንድነትን በማጎልበት ህዝቡ ብሄራዊ ጥቅሙን ለማስጠበቅ በጋራ እንዲቆም የሚያስችሉ ተግባራት ማከናወን ይገባል።

የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ የአፍራሽ ሀይሎችን እኩይ ተግባር ከማጋለጥ ባሻገር የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም አጀንዳ ያደረገ የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ላይ በሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዲኒር ዩሱፍ ብሄራዊ ጥምቅ እና ጂኦ ስትራቴጂክ ቁመና” ላይ ያተኮረ መነሻ ፅሁፍ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች እና ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሞያዎች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

amAmharic